"Love & Peace", Notes by Girma Yifrashewa

"Love & Peace", Notes by Girma Yifrashewa

1. The Shepherd With The Flute ዕረኛው ባለዋሽንት

This short piece is composed in such a way as to reflect the serene, simple rural life in Ethiopia. It also reflects Girma’s personal wishes to our world for love, hope and understanding. The theme is taken from a very popular and beloved composition “The Shepherd Flutist”, by the late Professor Ashenafi Kebede (1938-1998). The piano piece is dedicated Prof. Ashenafi Kebede who has made immense contribution to the growth of Ethiopian music.

ይህ አጭር የሙዚቃ ቅንብር የሚያንጸባርቀው የገጠራማውን የኢትዮጵያ ክፍል አስደሳች ተፈጥሮን ይዳስሳል፡፡ ግርማም በዚሁ የሙዚቃ መንፈስ ውስጥ የራሱን መልካም ምኞት ለምንኖርባት ዓለም ይመኛል፡፡ ፍቅርን፣ በጐነትን፣ ተስፋንና አንድነትን ያሳያል፡፡ ይህ ሙዚቃ መነሻነቱ ከፕ/ር አሸናፊ ከበደ “ባለዋሽንቱ እረኛ” ከተባለው ድርሰታቸው ዋናው ሃሳብ ተወስዶ ግርማም የራሱን ተጨማሪ ሙዚቃዊ ሃሳብ በማከል ለፒያኖ ያቀናበረው ነው፡፡ በዚህም መሠረት ግርማ ይህንን አጭር የፒያኖ ቅንብር ለፕ/ር አሸናፊ ከበደ ማስታወሻነት እንዲሆን ሲያደርግ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡

2. Chewata ጨዋታ

Chewata means fun times, friends gathered round the table and exchanging their views on a story which made them all very sad. But even though the story is sad, everyone is trying to make the other laugh. So in this composition, we find different personalities with an expression of their own under the blue cover.

ጨዋታ ማለት መዝናናት መደሰት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍን ያመላክታል፡፡ በዚህ ድርሰት ውስጥ አንድን ጽንሰ ሃሳብ ለማወደስ ይሞከራል፡፡ ይሄውም ብዙ ጊዜ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሳቅ የምንወድ እና የምናዘወትር ሕዝብ ነን፡፡ ይህን ታላቅ ተሰጥዖ በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በችግርና በሃዘንም ጊዜ መሳቅ መቀለድ እንደ አንድ መጽናኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግለናል፡፡ ይህ የፒያኖ ቅንብር ብዙ የተለያዩ ግለሰቦች በጠረጴዛ ዙሪያ ሆነው የሚያሳዝን ታሪኮችንና ክስተቶችን በማስታወስ እንዲሁም ለመርሳት ወይንም ያ ጊዜ እንዲያልፍ ቀልዶችን በማከል አሳዛኙን ጊዜ ያልፉታል፡፡ ይህ ድርሰት ብዙ ሳቅ፣ ቀልድ፣ ትረካ ወዘተ… ይሰሙበታል፡፡

3. Elilta ዕልልታ

Elilta is the fascinating vocal custom through which Ethiopians express their deepest joy. It is usually used during celebratory occasions such as weddings and other such social events. It is also widely used during church festivities. Elilta in this composition is an amalgamation of a popular wedding song and Girma’s personal interpretation of the unique sound of the piano.

በሀገራችን በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በተለያዩ ማህበራዊ እና ባህላዊ ግንኙነቶቻችን ውስጥ የተፈጥሮ ድምፃችንን በመጠቀም ደስታችንን እና እንዲሁም ምስጋናችንን የምናጐላበት ሙዚቃዊ አገላለጽ ነው፡፡

4. Sememen ሰመመን 

Sememen means half asleep, half awake, half dead, half alive. It utilizes one of the basic modes of Ethiopia music called “Anchihoyew lene”. The mode is widely used during the fasting period of the Ethiopian Orthodox Church and is said to embody a strong spiritual power.

ይህ አጭር የሙዚቃ ቅንብር ለማሳየት የሚሞክረው አንዳንድ ጊዜ በጥልቀት የእንቅልፍ ሂደት ውስጥ ሳንገባ በመንቃትና በማንቀላፋት መካከል እያለን ወይንም በቅዠት ውስጥ ሆነን የምንጓዘው ጉዞ ነው፡፡ ብዙም ልናስታውስ የማንችለው የሃሳብ ውጣውረዶች ነገር ግን በዛች ወቅት የጭንቀት ሂደት ውስጥ የሚያስገባን የሃሳብ መደበላለቅ ነው፡፡ ይህ የሙዚቃ ቅንብር መሰረት ያደረገው ከአራቱ እና በጣም ከታወቁት የሙዚቃ ቅኝቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና በተለይም ሙሉ ለሙሉ የመንፈሳዊ ዜማ መለገጫ በሆነው “አንቺ ሆየው ለኔ” በተባለው ቅኝት ውስጥ ነው””


5. Ambassel አምባሰል

Ambassel is the mountain in the northern part of Ethiopia (Wollo), the name also given to one of the four scales (modes) of Ethiopian music. Through this composition, Girma shows his admiration of mountains and the very peaceful surroundings.

በሰሜን ኢትዮጵያ በወሎ ክ/ሀገር አምባሰል የሚባል ተራራ እንዳለ ይታወቃል፡፡ በዜማና በግጥምም ይወደሳል፡፡ በሌላም በኩል አምባሰል ከአራቱ የሙዚቃ ቅኝቶች አንዱ ነው፡፡ ግርማም ለተራራ ያለውን ተፈጥሮአዊ ውበት በከፍተኛ ፍቅርና አድናቆት በዚሁ ድርሰት ውስጥ ይገልፀዋል፡፡ ተራራ ሰላም አለው፣ ተራራ ግርማ ሞገስ አለው፣ ተራራ ውበት አለው ወዘተ…